By Ídrís Ķoņńabà


ስለ ፈንቅል አላማው ግድ ባይኖረኝም፤ ነገርግን ለሚያራምዱት የፕሮፓጋንዳና ስለማያውቁት ታሪክ ውስጥ መግባታቸውን እየተዛብኩ ነዉ፥ አብዓላ በየትኛውም ታሪክ የትግራይ አካል ሆና አታውቅም!


ከታሪክ አንፃር ለመናገር ያክል፥ ትግሬዎች "አብዓላን ሽኸት ማለትን እንዴት እንደጀመሩትና አብዓላን መመኘት መቼና እንዴት እንደጀመሩ" እንነጋገር!

አብዓላ እንደ ማንኛውም የአፋር መሬት በጎሳ ባላባት ትተዳደር ነበር! የአፋር አከባቢዎች ከጎረቤት (እንዳርታ፥ ወጂራት) ወረራ ይካሄድበታል፥ አፋር በመሬቱ አይደራደርምና ጠላትን በመመከት አይታማም።


* አፄ ዩሃንስ "ያየኔ ኢትዬጵያ" ንጉስ ነግስት ሆኖ ስሾም፥ አብዓላ "ያኩሚ" (Yaakumi) የሚባል የመላ ሄርቶ ጎሳ (certoh- Affara-af) ባላባት ትተዳደር ነበር! ታዳ የአብዓላ መሬት አቀማመጥ ለወታደራዊ ስልጠና ምቹ መሆኑን የተረዳው አፄ ዩሃንስ "መሬቱን ለስልጠና ሰለሚፈልግ ፍቀድልኝ" ብሎ ወደ ያኩሚ

መልዕክት ላከ! ያኩሚ በበኩሉ "መሬቱ የመላ አፋር እንጅ እኔ ለብቻዬ የሚወስነው የለኝምና አማክራቸው፥ መልስ እሰጠሃለሁ!" አለው!


በዚህ የተናደደው አፄ ዩሃንስ "ማንንም ሳታስቀሩ

ጨፍጭፏቸው።" በማለት ትዕዛዝ አስተላለፈ "ሽኸቱ" በማለት! ትግሬዎች አብዓላን "ሸኸት" ማለት የጀመሩት በዛ የአፄ ዩሃንስ የጭካኔ ትዕዛዝ ነው። ያኩሚ በበኩሉ የንጉሱን ወታደር የሚመካበት የተደራጀ ሃይል ባይኖረውም፥ ለጠላት መንበረከክ ባህሉ አልነበረምና፥ በጀግንነት ተፋለማቸው፥ ከ39 ሺ እስከ 43 ሺ የሚገመት ህዝብ በጦርነቱ ተሰዋ! አላህ ይዘንላቸዉ!


* በደርግ ዘመን አፋሮች በአምስት የተለያዩ ግዛት ስር ተከለሉ፥ ቢሆንም ግን መሬታቸውን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም በማለታቸው አካባቢያቸውን በራሳቸው እንድያስተዳደሩ ተደረገ! በተመሳሳይ አብዓላን "ዓባስ አብድላ" ያስተዳድራት ነበር፥ ከሳቸው በኋላም ሀጂ ኢብራህም እስከ ህልፈታቸው አስተዳድሯታል።


~ እንደሚታወቀው በደረግ አገዛዝ ስር የደረሰው ጭቆና በመቃወም ለ17 አመታት መራራ ትግል ስያካሂዱ፥ በአንድ አስተዳደር ስር ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፥ በአጠቃላይ ማንነታቸው" ማስከበር ነበር። የደርግ አገዛዝ ተገርስሶ ኢህአዴግ ስመጣ ተቀዳሚ አላማው "የብሔር ብሔርሰቦች ጥያቄ" መመለስ በመሆኑ፣ አወቃቀሩ ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ባህልንም፣ የጋራ ሰነልቦናን ጭምር የሚያካትት ክልላዊ አወቃቀር ነው።


~ እዚ ጋ አንድ መስማማት ያለብን ነገር አለ! እሱም "የአፋር ክልል" ተብሎ አፋር እንደ ክልል ስዋቀር፥ በመጀመሪያ ደረጃ የታገሉለት አላማ መሆኑን ነው። በሁለተኛ ደረጃ የታገሉለት አላማ "ማንነታቸውን ማስከበር" መሆኑን ነው።

አፋር ደግሞ ማንነቱ "አፋሬ (Qafarre)" በሚባል መሰሶ ላይ የተመሰረተ ነው። አፋሬ ማለት "የአፋር" ማለት ስሆን በውስጡ "የአፋረኛ ቋንቋ፣ የአፋር ባህል፣ የአፋር ማድዓ(ህግ) እንድሁም

የአፋር መሬትን" ያካተተ ነው። ስለዚህ ዓፋር እንደ ክልል ስቋቋም እነዚህ አራት መሰረታዊ ነገሮች መነሻ በማድረግ ነው ማለት ነው።

በዚህ መነሻ አፋሮች፣ አፋርኛን እንደ ስራ ቋንቋ፣ ባህልን እንደ መለያ፣ የአፋር ህግን እንደ መዳኛ፣ እንድሁም የአፋር መሬትን እንደ መኖሪያ በመያዝ "የአፋር ክልል" ተብሎ በአምስት ዞኖች

ተዋቀረ ማለት ነው።

ስለዚህ የአፋር መሬት ከአፋር ማንነት ተነጥሎ የማይታይ "የአፋርነት" አንዱ መለያ ነው ማለት ነው።


*በመጨረሻም ኢህአዴግ ገባ፥ ኢህዴግ ስገባ አገሪቷን የተቆጣጠረው ህወሃት ነበር፥ ህወሃት ታዳ መሬቱ የማን እንደሆነና የሚያመጣዉ መዘዝ ስለሚያውቅ ብዙም ከመስመሩ ማለፍ አልፈለገም! ነገር ግን ስለ ታሪክ አይደለም ስለ ራሳቸውን ቤተሰብ ማንነት የማያውቁ የፈንቅል አስተባባሪዎች አብዓላ የትግራይ እንደነበረች አድረገው ይናገራሉ፥ ነገር ግን አንዳች ታሪክ አያቀርቡም አብዓላ የትግራይ እንደነበረች የሚያስመሰክር፥ እናም እላለሁ በመሬት ጉዳይ ድርድር አይታሰብምና በፍቅር አብሮ መኖር ከሆነ የኛ ባህልና እሴታችን ነዉ::