*************************
የአፋር ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ባደረባቸው ህመም የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው በ74 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈ ድረስ የአፋር ህዝብ ሱልጣን በመሆን አገልግለዋል።
ሱልጣን ሀንፈሬ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በመሆን የመሩ ሲሆን በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆንም ኢትዮጵያን አገልግለዋል።
የሱልጣን ሀንፈሬ ስርአተ ቀብር ነገ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም በአይሰኢታ ከተማ በሀደሌ ጌራ የሚፈፀም መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
0 Comments