#ፊኢማ
የሰው ልጅ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ደስታና ችግርን አብሮ በመካፈል ተረዳድቶና ተደጋግፎ ኖሯል፡፤
ይህ አብሮ የመኖር ባህሪው የሠው ልጅ በተናጠል ሊወጣው ማይችለውን ተፈጥሮአዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወቱ ዋስትና እንዲያገኝ ስላስቻለው ማንኛውም ህብረተሰብ በቁጥር ይብዛም ይነስም በጋራ ሲሆር ይስተዋላል፡፡
አሁን ባለንበት ቴክኖሎጂ ዘመን የመረዳደቱን መንፈስ አብሮ በመኖርና በቅርበት የሚወሰን ሣይሆን አንዱ አገር ከሌላው አገር እንዲሁም አንዱ አህጉር ከሌላኛው ጋር ጊዜና ቦታ ሣይወስናቸው አንድ ላይ ለመኖር ችለዋል፡፤
የመረዳዳት መንፈስን ከአገር ደረጃ በጣም ብቅ ብለን ስንመለከት ማንም ቢሆን ከጎረቤቱ ከቤተሰቡ ወይም ከአንዱ ማህበረሰብ ክፍል ጋር የግድ መቆራኘቱ አይቀሬ ነው፡:
ወደ ሃገራችን ሁኔታ ስንመለስ አንድ አይነት ባህልና ሃይማኖት ፆታ፣ አንድ አካባቢ መኖርና በአንድ አይነት የስራ መስክ ላይ መስማራትን መሰረት አድርጎ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተቀራርበው በመረዳደትና በመደጋፍ ይኖራል፡፡ እድር ፣ማህበር፣ጽዋ፣ ወዘተ የተለያየ ስያሜ በመስጠት 19 ይቀራረባሉ፡፤
አገራችን ኢትዮጲያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባት በመሆኗ አንድ ብሄረሰቦቿ ብዛት ባህልና ወጋቸውም የተለያየ ስለሆነ የመረዳዳትና አብሮ የመኖር ስርአታቸውም እንዲሁም የተለያየ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
የክልሉ ማህበረሰብ በተለይ የገጠሩ ህዝብ በእለት ተእለት ኑሮው የሚገጥሙትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቃለል የሚጠቀምባቸው ባህላዊ አሰራሮች ያሉት ሲሆን በደስታም ሆነ በሀዘን ፣በእርሻም ሆነ በቤት ስራ፣ በአንድ ሰው ጉልበት ሊሰራ የማይቻለውን ወይም አንድ ሠው ብቻውን ቢስራው ሊደርሰበት የሚችለውን ጉዳትና ኪሣራ በመቀነስ የጋራ ችግሮችን የሚፈታባቸውና የሚተጋገዝባቸው በውልና በአዋጅ ያልተቋቋሙ ባህላዊ ማህራዊ ህብረቶች በብዛት እንደነበሩባቸውና ዛሬም እንደሚጠቀሙባቸው ይታወቃል፡፡
ውላዊ ያልሆኑ ያላንዳች ሠነድና አዋጅ የሚደረገው ባህላዊ የመረዳደትና የመተባበር መልኮች መቼ፣ እንዴት እንደተጀመሩ ለማወቅ ጥረት ተደርጎ ትክክለኛ መልስ ለማግነት ባይቻልም እስካሁን በተገኘው መረጃ ከጥንት አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ መጥቶ ዛሬ ለዚህ ትውልድ መድረሱን ከብሄረሰቡ አባላት ለመረዳት ተችሏል፡፡
የአፋር ብሄረሰብ የራሱ የሆነ ባህላዊና ታካዊ ስርአት ባለቤት ሲሆን ይህ የማንነቱ መግለጫ የሆነው ባህል አሁንም እንደተጠበቀ ይገኛል፡፡
የብሄረሰብን ባህል ሙሉውን ለመግለጽ በቀላሉ የሚዘለቅ ባለመሆኑ ከመነሻችን የጠቃቀስነውን የመረዳደትና አብሮ የመኖር ባህል በአፋር ብሄረሰብ ምን መልክ እንዳለው ተይቀን ያገኘነውን እናቀርባለን፡፤
አቶ ሙሳ መሀመድ ይባላሉ በአፋር ክልል ባህል ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ የባህል መምሪያ ሃላፊ ናቸው፡፡
የአፋርን ባህል ጠንቅቀው የሚያውቁና በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ የስራ መስኮች ሲሰሩ የቆዩ የሞያ ባለቤት ናቸው፡፡
የአፋርን ብሄረሰብ የእደር ስርአት የሚገልጽልን እሣቸው ናቸው፡፡ በአፋር ብሄረሰብ ባህላዊ የቡድን አደረጃጀት ፊኢማ ይባላል፡፡ ይህም የብርቱ ወንዶች ስብሰባ የቡድን ስም ሲሆን የፊኢማ አባላት ሠላምና ‹‹ ›› ፀጥታን የማስከበር ፣ፍርድን ማስፈፀም ፣ የታመመን የመርዳት፣እንግዳን የማስተናገድ በሰርግና በመሰል በአላት ስራ የማገዝ፣ በቀብር ወቅት መቃብሩን የማዘጋጀትና ስርአቱን ማስፈፀም ወዘተ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
በእያንዳንዱ ጎሳበብርታታቸውና ንቃታቸው የተመረጡ ወንድ ወጣቶችና ጎማልሶች ተውጣጥተው ፊኢማ ይመሰርታል፡፡ ‹‹ ››
‹‹ ፊኢማ በመባል የሚታወቀው የአፋር ብሄረሰብ ማህበራዊ የቡድን አደረጃጀት በአንድ ሠው አቅም የማይወጡትን ስራዎች ተጋግዞ ለማቃለል ›› ብሄረሰቡ አባላት የሚጠቁሙበት ባህላዊ ቡድን ነው፡፤
ለስራ ተሣታዎችም ከስራ ባኋላ ባንድ ላይ መብላትና መጠጣጥም ያለ ነው፡፡
ከብሄረሰቡ ባህላዊ ማህራት መረዳዳት በችግር ጊዜ የሚፈለገውን በማዋጣት የተለያዩ ችግሮችን ለማቃለል በገንዘብ ፣በጎልበትና በምክር ድጋፎች ማድረግን ያጠቃልላል፡፤ ለመጥቀስ ያህልም ከብሄረሰቡ እጅግ ድሃ ወይም አቅም ዳካማ የሆነውን መልሶ ለማቋቋም በገንዘብና በአይነት ደጎማ ማድረግን፣ በሃዘን ወይም በቀብር ጊዜ ሃዘንተኛውን ማጽናናት፣ሃዘንተኞችን ማስተናገድና ማገልገልን ሁሉ ይጨምራል፡፡
በሰርግ ወቅትም ቢሆን ለጋብቻ የሚዘጋጀው ሰው በገንዘብ በኩል ለሚደርስበት ችግር በማዋጣት ለመፍታት የሚያገለግል አሰራር ነው፡፡
ከባድ ጉዳትና እስክ ሕይዎት መጥፋት የሚያደርጉት ግቦች በጋራ የመፍታት ፊኢማ ከቀላል እስከ በአገር ላይ ጥቃት ሲዘረዘር ለመከላከል ቅስቀሳ የማድረግ ሃላፊነትም አለበት፡፡
እንዲሁም የብሄረሰቡ አባላት የሆኑ ሴቶች ያለባቸውን የቤት ውስጥ እቃና የገንዘብ ችግር ለማቃለል አባላቱ ገንዘብ በማዋጣት በየተራ እንደ ችግራቸው ቅድሚያ እየተሰጣጡ ሁሉንም በየተራ የሚደርሣቸው የፋይናንስ የመረዳደረት ዘዴ ነው፡፤ የብሄረሰቡን አባላት በግል ለመስራት ያልቻሉትን ማንኛውም ከባድ ወይም ብዛት ላለው ስራ በዘመቻ መልክ በመስማራ የሚከናወን ባህላዊ የህብረት ስራ ነው፡፡
‹‹ ፊኢማ የእድር መንፈስ ቢኖረውም የአፋር ብሄረሰብ የመረዳደት ባህል ከሌሎች ብሄረሰቦች ለየት ይላል፡፡
የራሱ ባህልና ወግ አለው ፡፤
በአፋር ›› ብሄረሰብ ውስጥ ፊኢማ ሲባል ወንድና ሴት አይቀላቀልም ወንዶች የራሣቸው ፊኢማ ሲኖራቸው ሴቶችም እንዲሁ የራሳቸው ፊኢማ አላቸውው፡ እስከ 20 ዛሬ ድረስ የአፋር ብሄረሰብን ባህል እድሜ የሰጠው ከጥንት አያትና ቅድመ አያቶች ጀምሮ እየተወራረሰ የመጣው የፊኢማ ባህል እንደሆነ አቶ ሙሣ ይገልፃል፡፡
‹‹ ፊኢማ አጠቃላይ ጽንስ ሃሣቡ በመረዳደት ላይ በመመርኮዝ በሞት፣ በሰርግና በአባላት ላይ ችግሮች ሲከሰቱ የሚከናወን ነው፡፤
በጽሁፍ የአፋር ›› ደንብና ስርአት ባይኖርም ከጥንት ጀምሮ በቃል ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ደንብ ለመሆኑ አቶ ሙሣ ይናገራሉ፡፡
ፊኢማ በአባላቱ እውቅና የተሠጠው አለቃ/ሰብሣቢ ይኖዋል፡፡ በስብሰቢው አማካይነት ህግና ደንብ ያልተከተለ አባል ይቀጣል፡፡
ስለዚህ አባላት ለደንቡ ተገዥ በመሆን አለባቸው፡፡
በአፋር ብሄረሰብ ብዛት ያላቸው ፊእማዎች አሉ፡፡
ማንኛውም የብሄረሰብ አባል በመረተው ፊኢማ የመግባት መብት አለው፡፤ ሆኖም ግን ከነበረበት ፊእማ ወጥቶ ወደ ሌላ ፊእማ ለመግባት ከመጀመሪያው ፊእማ ለምን እንደወጣ በቂ ምክንያት ካለቀረበ ሌለኛው ፊኢማ በአባልነት አይቀበለውም ፡፤
ቀደም ሲል እንደተገለፀው ፊእማዎች የወንድና የሴት ከመሆናቸው ሌላ አንዱን ፊእማ ከሌላው የሚለየው ባህሪ የለም ሴቶች የራሳቸው ደንብ አላቸው ወንዶቹም እንዲሁም፡፡
የሴቶች ፊእማ ላይ በማተኮር ለሰርግና ለለቅሶ ጊዜ ምን መልክ እንዳለው አቶ ሙሣን ጠይቀናቸው ነበው፡፡ ሰው በሞሞትበት ጊዜ ፣ፊኢማው ‹ ›› ይጠራል፡፡ በዚህም ጊዜ የተለየ አለባበስ ባህል አለ ወደ ለቅሶ የሚመጡ ሴቶች ሁሉ በፀጉራቸው ላይ ሻሽ ያስራሉ ባዶ እጃቸውን አይመጡም ፡፤ ይህም የሚደረገው ሀዘንተኛውም ሆነ ዘመዶቹ ምንም አይነት ወጭ እንዳያወጡና ፊእማው ከጎናቸው መሆኑን ለማሣወቅ ነው፡
ሠርግንም በተመለከተ በፊእማዎች በኩል ጥሪ ይደረጋል በሰርግ ጊዜ ብቻ የሚዘፈን ባህላዊ ጨዋታ ይጫወታሉ፡፤
በጭፈራውም ወቅት ፊእማው ቀድሞ ባይቸወት ሌላ ሠው መጫወት አይችልም፡፤ ቀድሞ የሚጫወት ሌላ ካለ ይቀጣል፡፡
ጨፍረው ከዘመድ አዝማድ ፊኢማ ‹‹ ›. ከፍተኛ ክብር ስላለው በድግሱ ወቅት ከአባላት የሚዘጋጅላቸው ምግብ የተለየ ነው፡፡ የሚሆነው፡፤
የሴቶች ፊእማ ባህልንም ከማስጠበቁ አኳያ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው ማንኛውም የአፋር ብሄረሰብ እናት ይቀርበኛል የስማማኛል ከምትለው ፊእማ መግባት የግድ ነው ፡፡
የፊኢማ ስርአቱ ከመረዳደትና ከመደጋገፍ ባሻገር የብሄረሰቡን ባህልና ወግ የሚጠብቅ በመሆኑ ከሌሎች ባህላዊ ማህበራት የተለየ ያደርገዋል ፡፡ ፊእማ አንድ ብሄረሰብ አፋርን ብቻ የሚወክል ሲሆን ችግርንም ሆነ ደስታን የብሄረሰቡ አባላት ብቻ ተረዳድተውና ተደጋግፈው የሚወጡበት ነው፡፡
ስለዚህ በአጠቃላይ ከፊእማ ደንብ ውስ የአለባበስ ስርአቱ፣ አመጋገቡ ሰርግና ሀዘኑ እንዲሁም ማህበራዊ ተራክቦው በአባላቶቹ ዘንድ አፋርን የመምሰል ግዴታ አለበት፡፤
በአጠቃላይ ፊእማ የአፋር ብሄረሰብን ያስተሣሠረና የማንነቱ መግለጫ ስለመሆኑ አብዛኛው የብሄረሰቡ አባላት አፀንኦት ሰጥተው ነው የሚናገሩት ፡፡
ታዲያ ይህ አኩሪ የሆነው ባህላቸው አሁንም ቢሆን በቃል ቅብብሎሽ የሚወርድ ነው፡፡
ባህሉንና ስርአቱን ጠንቅቀው የሚውቁ በእድሜ የገፋ ሰዎች ባለፋ ቁር ለተተኪው ትውልድ ይህ ባህል ሣይጓደል እንዴት ነው የሚተላለፍው የሚለው ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በቃል ያለ ይረሣል በጽሁፍ የሰፈረ ይወረሣል፡፡ ነውና የሚመለከታቸው አካላት ቢያስቡበት እንላለን፡፡
https://afar-cultural.com
©2020 Afar culture | All Rights Reserved
1 Comments
Great Youth Structure
ReplyDelete