የኢትዬጵያ ብቸኛ መዳኛ መንገድ…?


 የኢትዬጵያ መዳኛ ብቸኛ መንገድ… ፌዴራሊዝሙን ማጥፋት ነው ለሚሉ ወገኖች የተወሰነ ነገር ለማለት ያክል…! ደርግ የሚባል ፋሽስት ሀይል ነበር። በመዋቅሩ አሃዳዊ የሆነ። እናም የትግራይ ኃይል ፀረ ደርግ ትግል ለማድረግ ጫካ ገባ። የአፋርም የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች "ራስን በራስ የማስተዳደር መብት" ጥያቄ የሚያራምዱ ኃይሎች በተመሳሳይ መልኩ። ከዛ ቀደም ብሎ የኤርትራ ነፃነት ታጋዬች ትግል ላይ ነበሩ። ደርግ ወንበዴ አላቸው። ፀረ ኢትዬጰያ፣ ገንጣይ አስገንጣይ… ወዘተ! እናም ጥያቄውን በኃይል ለማፈን ሞከሩ። ብዙ አመታትን የፈጀ የ‘ርስ በርስ ጦርነት ተካሄደ። በመጨረሻም ደርግ ተሸነፈ። ጥያቄውን በኃይል ለማፈን በተደረገው ሙከራ ኤርተራም ሄደች። "ወያኔም አሸነፈች"። ወያኔ ግን በፖለቲካ የነበራት ሚና፣ በኃያላን ዘንድ ያገኘችው እውቅናና የውትድርና ብቃቷ ብቻ አይደለም እንድታሸንፍ የደረጋት። የኢትዬጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዋናነት የትግል አጋር ሰለነበሩ እንጅ። ከወያኔ ያልተናነሰ መስዋዕትነትን በመክፈላቸው እንጅ። ======== አሁን ላይ ድጋሜ ተመሳሳይ ጦርነት ተነሳ። ወያኔ የፌዴራል መንግስቱን ለመጣል ሞከረ። ልክ እንደ ደርግ ጊዜ። በተመሳሳይ የውጭ ድጋፍ አላቸው። የውትድርና አቅምና ብቃት አላቸው። ግን… ወሳኝ የሆነ ነገር የላቸውም። የብሔር ብሔረሰቦች ድጋፍ። እናም ወያኔ ደብረብርሀን ደርሶ ወደ ክልሉ እንድፈረጠጥ ያደረገውና ለሽንፈታቸው ዋና መንስኤ የሆነው የብሔር ብሔረሰቦች ድጋፍ ባለማገኘታቸው ነው። አንድ ሰው አሁን ላይ ወያኔ አፋርን ብቻ ከጎኑ ማሰለፍ ብችል ምን ልፈጠር ይችል እንደነበረ ማሰብ ከቻለ ምን እያልኩ እንደሆነ ይገበዋል። ዘር ዘር ላድርገው መሰለኝ። የአማራ ክልል በተጨነቀ ግዜ፣ ባህርዳር አደጋ ውስጥ የገባ በመሰላቸው ጊዜ የድረሱልን ጥሪ ያደረጉት ለ"ብሔር ብሔረሰቦች" ነበር። ወያኔም አድስ አባባ እየገቡ እንደሆኑ ባመኑ ግዜ ዲሲ ላይ "የፌዴራሊስትና የኮንፌዴራሊስት ኃይል" ያላቸውን የብሔር ቡድኖች ወደ ማቋቋም ነበር የገባው። ያው ስከሽፍበት አሁን ረሷቸው እንጅ። ይህ በአጭሩ የኢትዬጵያ የአደጋ ግዜ ደራሽ "ብሔር ብሔረሰቡ" መሆኑን ተግባራዊ ማሳያ ነው የሆነው። ይልቅ "አሃዳዊ ኃይሎች" ነፍስ የሚዘሩት በድህረ ጦርነትና በፖለቲካዊ ሽግግር ግዜ ነው። ትርጉሙ ይገባችኋል። እናም ወያኔ ያኔ እንድያሸንፍም አሁን እንድሸነፍም ምክንያት ከሆኑት ሦስቱ ዋና ዋና ምክንያቶቸ አንዱ ቫረዬብል ብቻ ወሳኝ መሆኑን በግልፅ የታየ ይመሰለኛል። ማለትም የውጭ ኃይል ድጋፍ፣ የውትድርናና የፖለቲካ አቅም፣ የብሔር ብሔርሰቦች ድጋፍ። ኮዝ ሳይቀየር። ያው ደርግን ያስወገደው፣ ወያኔን ከስልጣን የገፋው፣ መልሶ ልመጡ ስሉ ያባረራቸው… ብሔር ብሔረሰቡ ነው። የፌዴራል ስርአቱ ነው። ታዳ በተግባር ኢትዬጵያን ያዳነው ይህ ስርአት አይደለምን? ======== ይልቅ የምንስማማባቸው ነገሮች አሉ። የከረረ ነገር አለ? አዎ። ፅንፍ የያዘ ነገር አለ? አዎ። ይህ እንድሆን የፌዴራል ስርአቱ አስተዋፅዖ አበርክቷል? አዎ። እለሃለሁ። ግን ወያኔ መች በትክክል ፌዴራሊዝሙን ተገበረ? ብዬ መልሼ እጠይቀሃለሁ። መጀመሪየም ፌዴራሊዝሙ ብተገበር ኑሮ ዋናው "የፌዴራሊስት ካምፕ" የሆኑት ኃይሎች ለምን አባረራቸው? ብዬ እለሃለሁ። ይልቅ እውነታውን ልንገርህ። ኢትዬጵያ የባህር በር ያሳጣት የወያኔ ሴራ ብቻ ሳይሆን የደርግ መንግስት አፈናም እንደ መንስኤ የሚታይ ነው። የጦርነቶቹ መንስኤዎች በዋናነት ጥያቄዎቹን በኃይል ለማፈን የሚደርግ የአሃዳዊነት አስተሳሰብ ነው። ኢሳያስ የተሻለ ኤርትራን መሰረትኩ ስል የፈጠረው ትግረኛ ተናጋሪ ኤርትራን ነው። ግን ደግሞ ሰው አልባ፣ ኢኮኖሚ አልባ አገር። (አቶ ኢሳያስ "የፌዴራሊዝም ስርአት ለኢትዬጵያ አደጋ ነው"ስል ለኢትዬጵያ አስቦ ሳይሆን ኤርትራ ላይ ያለው የረስን በራስ የማስተዳደር መብት ጥያቄን ውድቅ ለማድረግ እንደ ጄስቲፊኬሽን ማምጣቱ ነው። ለኤርትራ አሃዳዊነት ምን ጠቀመ ብንል መልስ ኑሮት አይደለም።) በአፈናው የብሔር ጥያቄ ያነገቡ ኃይሎች ተፈጥሯል። ድህረ ኢሳያስ ያለችው ኤርትራ በተመለከተ አሰፈሪ ሰናሪዬዎች የሚነሱት እሱ አፈንኩ ብሎ ከሚያስበው ከብሔርና ከሐይማኖት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ነው። ===== ይልቅ… አሁን መታሰብ አለበት ብዬ የማስባቸው ሁለት ነገሮች አሉ። 1ኛ: ከወትሮ በተለየ ሁኔታ የመሀል መንግስትና የዳር ክልል መሀል በተደረገው ጦርነት ሁሉም ክልሎች ከመሀል መንግስት ጎን ተሰልፏል። ይህ እንድሆን ያስቻለው ወደ መሬት በደንብ ያልወረደው ሃሳባዊው ፌዴራሊዝም ስርአት ነው። ወደ መሬት ወርዶ በነበረ፣ ጦርነቱን ራሱ ማስቀረት ይችል ነበር ለማለት ያስደፍራል። ስለዚህ ስርአቱ በደንብ ወደ መሬት ወርዶ በዘላቂነት የመሃልና የዳር ፍጥጫ እንድቆም በሚያስችል መልኩ ማስቀጠል አለብን። 2ኛ: ያሁኑ ጦርነት አንዳንድ የፌዴራሊስት ኃይሎችን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል። የፌዴራል መንግስትና ክልሎች መሃል ያለው ግንኙነት መጤን አለበት ከሚሉ ጀምሮ ጭራሽ ኮንፌዴራሊዝም አስተሳሰብን እንደ አማራጭ እስከሚያራምዱ ደረስ… ከዚህም ከዛም ብቅ ብቅ እያሉ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን… ፌዴራል ላይ የስልጣን ቁንጮ የሚይዙ ቡድኖች ከአሃዳዊነት ባልተናነሰ ሁኔታ ሁሉንም ነገር ማዕካለዊ በማድረግ ፌዴራሊዝሙ ወደ መሬት እንዳይወርድ እንቅፋት እየሆኑ ሰለሆነ ጠንከራ ክልሎችና ደከም ያለ ፌዴራል መንግስት አሰራር መከተል አለብን የሚሉም አሉ። በመሆኑም መሰል አስተሳበሰቦች የሀገርቱን አንድነት ላይ ልያመጡ የሚችሉ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ከግምት በማስገባት ወደ መሀል እንድመጡ ማድረግ የፌዴራሊስት ካመፕ ትልቅ የቤት ስራ ሆኖ ብቅ ብሏል። ካልሆነ ፌደራሊዝሙ የተፈለገበት ዋና አላማ ሰለሚስት ውጤቱ ተቃራኒ ይሆናል። Bunaytu! 

Facebook: https://www.facebook.com/mayasin3