አረቦች አንድ አባባል አላቸው። "ዸራበኒ ፋባካ፣ ወሰበቃኒ ፋሽታ ካ" የሚል። ግርድፍ ትርጉሙ "ደብድቦኝ ራሱ አለቀሰ፣ ቀድሞኝም ከሰሰ" የሚል ነው። ይህን አባባል መጠቀሜ የወያኔን ድርጊት በደንብ ሰለሚገልፅልኝ ነው። በተለይ ደግሞ ያሁኑ የአብዓለ ጉዳይ በተመለከተ ያወጡት መግለጫ ሳነብ።
አብዓላ ላይ የሆነው ሌላ አይደለም። ሌሎች አካባቢዎች ላይ ስያደርጉ እንደነበሩት ነው። ግን ተጨማሪ ነገር ነበራቸው። ብዙ አባላት ከተማ ውስጥ አላቸው። ጂኦግራፊው ለነሱ የተመቸ ነው። ከተማው ለመቀለ ቅርብ በመሆኑ ሰው ኃይልም ሎጂስቲክም አይቸገሩም። እናም "ሰልፊ" ሳያስፈልጋቸው ከተማውን መያዛቸው እርግጠኛ እንደሆኑ አሰቡ። በዚህ የተሳሳተ ስሌት ነው በጠረራ ፀኃይ ነዋሪ መስሎ በግራና ቀኝ ከተማውን በድንገት ለመክበብ የሞከሩት። ለተወሰነ ሰዓታት ብቻ ነበረ እንዳሰቡት የሄደላቸው።
በዛ በተወሰነ ሰዓታት የፈፀሙት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ግን የጭካኔያቸው ጥግና ክፉ ሃሳባቸውን ግልፅ ያሳየ ነበር። እንደሚታወቀው አብዓላ ከተማ "ወደ ትግራይ መካለል አለባት" ብሎ በግልፅ የሚንቀሳቀስ ኃይል ያለበት ከተማ ነው። እውነት ኑሯቸው ሳይሆን ያው እነሱ ሰለነበሩ። እንቅስቃሴው ደግሞ ቀስ በቀስ በትጥቅ የታገዘ ሆኖ ነበረ። እናም አሳቻ ሰአት ጠብቆ መነሳት ካሁን በፊት የሚታወቁበት ነው። ያሁኑ ግን በጣም የተደራጀና ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ አብዓላን ከአፋር እጅ ለመንጠቅ ቆርጦ የተነሱበት መሆኑ የተጠቀሙት ስልት፣ ያሳዩት ጭካኔ፣ ማሳያ ነበር። የሚያሳዝነው ነዋሪውን በሙሉ ጨፍጭፎ ከተማውን ለመያዝ ነበር ሙከራቸው። ተራራ ላይ ሆኖ ወደ ከተማ የወረወሩት ትላልቅ መሳሪያ ህዝቡ ላይ እንደ ዝናብ ነበር የወረደው። ህፃናት፣ ሴቶች፣ ሽማግሌዎች፣ እንስሳት ሳይቀር ነበር የተጨፈጨፈው። በነገራችን ላይ ሰለማዊ ነዋሪ የሆነው ተጋሩም ሳይቀሩ ተጨፍጭፏል። ሰላማዊው ትግራዋይ ሞት ሰለማያስጨንቃቸው። ደግሞም በኋላ ላይ " Tigray genocide" ለማለት እንድመቻቸው። ራሳቸው ገድሏቸው ልያለቅሱላቸው! አላህ ያንዓልሁም!
ለማንኛውም እንደገመትነው አልቀረ። በጦርነቱ መሸነፋቸው ስያረጋገጡ "አብዓላ ላይ ተጋሩ ተጨፈጨፉ" በማለት ለቅሶ ጀመሩ። ያው እንደተለመደው ለህዝባቸው ስሆን አፋሮች አሸነፉን ላለማለት፣ ለነጮቹ ስሆን ለቅሶው ተሰሚነት እንድያገኝ በሚል "የኤርትራ ወታደሮችና የመከላከያ ኃይል ህዝባችን ጨፈጨፉ" በማለት ሪፖርት አደረጉ። በቅርቡ Amnesty international እና CNN መዘገባቸው ሰላማይቀር እየጠበቅን ነው።
ለማንኛውም ጭፍራ ላይ፣ ከሳጊታ ላይ፣ ሃዳሌኤላ ለይ፣ ያሎ ላይ፣… ወዘተ እንደሆነው ሁሉ… ትምህርት ተሰጥቷቸዋል። የተረፈው ወደ መቀለ ተሸኝቷል። ግን ከተማው ከመቀለ በጣም ቅርብ የሚባል ርቀት ላይ ሰለሚትገኝ ቶክሱ ብቆም ለሰዓታት ብቻ ነው። ይሸኛሉ፣ ይመለሳሉ። ቁጥር ሰለሆኑ!
እናም እንላለን።
ለመንግስታችን: ጦርነቱን ያቆመው መከላከያ ብቻ ይመስላል። ወያኔዎች ያቆሙት ወደ አድስ አበባ ማሰብ ብቻ ይመስላል። እናም እንደ አብዓላ ያሉ ድንበር ከተሞች ጉዳይ መፍትሔ ይሻል። ወለም ዘለም ማለት ድንበር አካባቢ ያሉ ህዝቦችን ይጎዳልና!
ለወያኔ: በአፋር በኩል የሚደርስባችሁ ሽንፈት "አፋሮች አሸነፉን" ላለማለት በሚል "የኤርትራ ወታደሮች" ጨፈጨፉን የሚትሉት ነገር ቀጣይ ትውልድ "ኤርትራ" ስባል የሚሸሽ እንድሆን እያደረጋችሁ እንደሆነ አትርሱ። አፋር እንደሆነ ድሮም በሜዳ እንጅ በዜና አሸንፎ አያውቅም። ያው ፈሪ ጎረቤት እንዳይኖረን ብዬ እኮ ነው። ;)
© Muhammed A. Yassin
Abala City, The Capital of Northern Zone (2) Afar |
0 Comments